Pspየመግቢያ ሞጁል ይህ የግላዊ መግለጫ በ Microsoft ድርጣቢያ፣ ዳታ በሚሰበስቡ እና እነዚህን ስምምነቶች በሚያሳዩ፣ እነዲሁም በእነሱ የመስመር ውጪ የምርት ድጋፍ አገልግሎቶች ላይ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ በእኛ ይህንን መግለጫ በማያሳዩ ወይም በማያገናኙ ወይም ደግሞ የራሳቸው የግላዊነት መግለጫዎች ካላቸው የMicrosoft ጣቢያዎች፣ አገልግሎቶች እና ምርቶች ላይ ተግባራዊ አይደረግም፡፡
አብዛኛዎቹ Microsoft ጣቢያዎች "ኩኪዎችን" ይጠቀማሉ፣ በድር ሰርቨር የሚነበቡ የሚችሉ ጥንሽ ጽሁፍ ፋይል ሆነው በእረስዎ በሀርድ ድራይቭ ላይ ኩኪ የሚያስቀምጡ ናቸው። የእርስዎን ምርጫዎች እና ሴቲንጎች ለማከማቸት፤ ለመግቢያ እርዳታ፤ የታለመ ማስታወቂ ለማቅረብ፤ እንዲሁም የጣቢያ አሰራርን ለመተንተን ኩኪዎችን ልንጠቀም እንችላለን።
በተጨማሪም የኩኪዎችን ስርጭት ለመርዳት እና አናላይቲኮችን ለመሰብሰብ የድር ቢኮኖችን እንጠቀማለን። እነዚህ ምናልባት የእርሶን የግል መረጃ ከመሰብሰብ የተከለከሉ፣ የሶስተኛ ወገን ቢኮኖችን ሊጨምሩ ይችላሉ።
እርስዎ ኩኪዎችን እና ተመሳሳይ ትክኖሎጂዎችን ለመቆጣጠር የተለያዩ መሳሪያዎች አሎት፣ እነዚህም:
የኩኪዎች አጠቃቀማችን
አብዛኛዎቹ የ Microsoft ድር ጣቢያ ትንንሽ የጽሁፍ ፋይሎች በድር አገልጋይ በሃርድ ዲስኮ ላይ ለማስቀመጥ ኩኪዎችን ይጠቀማሉ። ኩኪዎች ለእረስዎ ኩኪዎችን የሰጠው ዶሜን ውስጥ የሚገኘው በድር አገልጋዩ ሊነበብ የሚችል ጽሁፍ ይዛዋል። ያም ጽሁፍ ብዙውን ጊዜ በልዩ ሁኔታ ኮምፒውተሮን መለየት የሚችሉ ተከታታይ አሃዞችን እና ፈደላትን ይይዛል፣ ነገርግን ሌሎችም ረጃዎችን ሊይዝ ይችላል። አንድ ድር ጣቢያን ሲጎበኙ በርስዎ ሃርድ ዲስክ ውስጥ Microsoft ሊያስቀምጣቸው ከሚችላቸው ኩኪዎች ውስጥ አንድ ምሳሌ እነሆ፦ E3732CA7E319442F97EA48A170C99801
ኩኪዎችን ለሚከተለው መጠቀም እንችላለን፦
አብዛኛዉን ጊዜ የምንጠቀማቸው ኩኪዎች ውስጥ አንዳንዶቹ በሚከተለው ቻርት ውስጥ ተዘርዝረዋል። ይህ ዝርዝር ሁሉን ያካተተ አይደለም፣ ነገር ግን ኩኪዎችን ከምናዘጋጅባቸው ምክንያቶች ውስጥ የተወሰኑትን ለማሳየት የተዘጋጀ ነው። ከድር ጣቢያዎቻችን ውስጥ አንዱን ከጎበኙ፣ ጣቢያው ከሚከተሉት ውስጥ የተወሰኑትን ወይም ሁሉንም ኩኪዎች ሊያዘጋጅ ይችላል፦
ከኩኪዎች በተጨማሪ የእኛን ጣቢያ ሲጎበኙ Microsoft ሊያስተካክል ይችላል፣ እንደዚሁም Microsoft ጣቢያዎችን ሲጎበኙ ሶስተኛ አካል የተወሰኑ ኩኪዎችን ሊያስቀምጥ ይችላል። በተወሰኑ ጉዳዮች፣ ምክንያቱም እንደ ጣቢያ አናላይቲኮችን የመሳሰሉትን እኛን ተክቶ አገልግሎት እነዲሰጥ ሶስተኛ አካል እንመርጣለን። በሌሎች ሁኔታዎች፣ ምክንያቱም ጣቢችን በሌላ የማስታወቂያ መረብ የሚተላለፉ እንደ ቪዲዮዎች፣ የዜና ይዘት ወይም ማስታወቂያዎች የመሳሰሉት የድር-ገጾቻችን ከሶስተና ወገን ይዘቶችን ወይም ማስታወቂዎችን ሊይዝ ይችላል። ምክንያቱም መቃኛዎ ያንን ይዘት ለማስታወስ ወደ እነዚህ የድር አገልጋዮች ሊያገናኝ ይችላል፣ እነዚያ ሶስተኛ አካላት በሃርድ ድራይቮ ላይ የእራሳቸውን ኩኪዎች ለማስቀመጥ ወይም ለማንበብ ያስችላቸዋል።
ኩኪዎችን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል
ለምሳሌ፣ ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር 9 ውስጥ፣ የሚከተሉትን እርምጃዎችን በመውሰድ ኩኪዎችን ማገድ ይችላሉ፡
በሌሎች አሳሾች ላይ ኩኪዎችን መሰረዝ የሚችሉባቸው መንገዶች በሚከተለው ውስጥ ይገኛሉ http://www.allaboutcookies.org/manage-cookies/።
ኩኪዎችን ለመገደብ ከመረጡ በኩኪዎች ላይ ወደ ተመሰረቱ ሌሎች የMicrosoft መስተጋብራዊ ባህሪያት መግባት እና እነሱን መጠቀም ላይጠቀሙ እንደሚችሉ ያስተውሉ። በተጨማሪም በኩኪዎች ላይ የተመሰረቱ አንዳንድ የማስታወቂያ ምርጫዎች ላይከበሩ ይችላሉ።
Microsoftለምሳሌ ፣ ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር 9 ውስጥ፣ የሚከተሉትን እርምጃዎችን በመውሰድ ኩኪዎችን ማገድ ይችላሉ፡
እባክዎ ኩኪዎችን ለመሰረዝ ከመረጡ በኩኪዎቹ ቁጥጥር ስር ያሉ ሌሎች ቅንብሮች እና ምርጫዎች፣ የማስታወቂያ ምርጫዎችን ጨማሮ፣ ሊሰረዙ እና ተመልሰው ላይገኙ እንደሚችሉ ይወቁ።
"ለአትከታተል" እና ለመከታተል ጥበቃ የአሳሽ መቆጣጠሪያዎች። አንዳንድ አዳዲስ አሳሾች "አትከታተል" ባህሪያትን አካተዋል። ከእነዚህ ባህሪያት አብዛኛዎቹ ባህሪያት ሲበሩ ወደሚጎበኟቸው ድር ጣቢያዎች እንዲከታተሉዎ እንደማይፈልጉ የሚጠቁሙ ሲግናሎችን ወይም አማራጮችን ይልካሉ። እነዚያ ጣቢያዎች (ወይም በእነዚያ ጣቢያዎች ውስጥ ያሉት የሶስተኛ ወገን ይዘቶች) ምንም እንኳን ይህንን ምርጫ የገለፁ ቢሆንም እርስዎ እንደ መከታተል ሊያዩዋቸው በሚችሉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፋቸውን ሊቀጥሉ ይችላሉ።
Internet Explorer 9 እና 10 የሚጎኟቸው ድር ጣቢያዎች ስለ ጉብኝትዎ ዝርዝር መረጃዎችን ለሶስተኛ ወገን ይዘት አቅራቢዎች በራስ ሰር እንዳይላኩ ለመከላከል የሚያስችል የመከታተል መከላከያ የተባለ ባህሪይ አላቸው። የመከታተያ ጥበቃ ዝርዝር ሲያክሉ፣ Internet Explorer ኩኪዎችን ጨማሮ ሶስተኛ ወገን ይዘቶችን እንዲታገድ ከተዘረዘረ ማንኛውም ጣቢያ ላይ ያግዳል። ወደነዚህ ጣቢያዎች ሚደረጉትን ጥሪዎች በመገደብ፣ Internet Explorer እነዚህ ሶስተኛ ወገኖች ስለርስዎ የሚሰበስቧቸውን መረጃዎች ይገድባሉ። የመከታተል ጥበቃ ዝርዝርዎን ሲያነቁ፣ Internet Explorer የአትከታል ሲግናሎችን ወይም አማራጮችን ወደሚጎኟቸው ጣቢያዎች ይልካል። በተጨማሪም፣ በInternet Explorer 10 ውስጥ ከፈለጉ DNT ለብቻው "ማጥፋት" ወይም "ማብራት" ይችላሉ። ስለየመከታተልጥበቃዝርዝሮችእናአተከታተልተጨማሪመረጃለማግኘት፣ እባክዎ Internet Explorer ግላዊነትመግለጫ ን ወይም Internet Explorer እገዛ ን ይመልከቱ።
የግል ማስታወቂያ ካፓኒዎች የራሳቸውን የመምረጫ ማስቻያዎችን በተጨማሪም በላቀ ሁኔታ የተሻሻለሉ የማስታወቂያ ምርጫዎችን ሊያቀርቡ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ የማይክሮሶፍት ማስታወቂያ ምርጫ እና መከላከያ መቆጣጠሪያዎች በ http://choice.live.com/advertisementchoice/ ላይ ይገኛሉ። እባክዎን መከላከል ማለት እርስዎ ማስታወቂያዎችን ማግኘት ያቆማሉ ወይም ጥቂት ማስታወቂያዎችን ይመለከታሉ ማለት እንዳለለሆነ ይገንዘቡ፤ ነገርግን መከላከል ካደረጉ፣ ከዚያ በኋላ እርስዎ የሚቀበሏቸው ማስታወቂያዎች በባህሪያቸው የተነጣጠሩ አይሆኑም። በተጨማሪም፣ ላለመቀበል መምረጥ መረጃ ወደ አገልጋያችን እንዳይሄድ አያግደውም። ነገር ግን ለባህሪይ ተኮር ማስታወቂያዎች የምንጠቀማቸውን መገለጫዎች እንዳንፈጥር እና እንዳናዘምን ያደርገናል።
የድር ቢኮኖች አጠቃቀማችን
የMicrosoft የድር ገፆች ዌብ ቢኮኖች የተባሉ - አንዳንድ ጊዜ ባለነጠላ-ፒክስል ስጦታዎች በመባል የሚታወቁ - ኤሌክትሮኒክ ምስሎችን ሊያካትቱ ይችላሉ። እነሱም በጣቢያዎችዎ ውስጥ ያሉ ኩኪዎችን እንድናቀርብ ለማገዝ፣ ገፆቹን የጎበኙትን ተጠቃሚዎች ለመቁጠር እንዲሁም በጋራ የንግድ ስም የተሰጣቸው አገልግሎቶችን እንድናቀርብ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። መልእክቶች መከፈታቸውን እና እየተከወኑ መሆናቸውን ለመለየት ድር አበረታቾችን በማሰተዋወቂያ ኢ-ሜይል መልእክቶች ወይም በእኛ ኒውስሌተር ልናካትት እንችላለን።
በተጨማሪም በMicrosoft ጣቢያዎች ላይ ከሚያስተዋውቁ ሌሎች ኩባንያዎች ጋር በጣቢያቸው ላይ ወይም በማስታወቂያዎቻቸው ላይ የድር ቢኮኖችን ለማስቀመጥ በጋራ ልንሰራ እንችላለን። ይህም በMicrosoft ጣቢያ ላይ የወጡ ማስታወቂያዎችን ጠቅ ማድረግ ምን ያህል ጊዜ በአስተዋዋቂው ጣቢያ ላይ ግዢዎችን ወይም ሌሎች ድርጊቶችን እንደሚጋብዝ ስታቲስቲክስ ለማዘጋጀት ይጠቅመናል።
Microsoft ስለንግድ ማስታወቂያችን ብቁነት ወይም ስለሌሎች የእኛ ጣቢያዎች ትግበራዎች የተጠናከረ ሰታትስቲክስ እንድናዋቅር ለመርዳት ድር አበረታቾችን ከሶሰተኛ ወገን ያካትታል። እነዚህ የድር አበረጣቾች በኮፒውተሮ ላይ ሶስተኛ አካል ኩኮዎችን ለማስቀመጥ ወይም ለማንበብ ይረዱታል። እኛ ሶስተኛ አካል የእርስዎን መረጃ ከእኛ ጣቢያዎች ለመሰብሰብ ወይም ለማየት እነዳችል እንከለክላለን። ሆኖምግን ፣ የሚከተሉትን የእያንዳንዳቸውን አናላይቲክ አቅራቢ ማገናኛ ላይ ጠቅ በማድረግ ከመረጃ ስብሰባ ወይም በእነዚህ ሶስተኛ አካል አናላይቲክ ካምፓኒዎች ጠቀሜታ ላይ ከመዋል መከላከል ይችላሉ፥
ከመደበኛ ኩኪዎች እና ድር አበረታቺች
በተጨማሪ ሌሎች ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች፣ ድረ-ገጽ በኮመፒዉተሮ ላይ የዉሂብ ፋይሎችን ለማከማቸትን ለማንበብ ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን ይጠቀማል። የህ የእረስዎን ፍላጎት ለመጠበቅ ወይም ፍጥነትን እና ክንዋኔን ለማሻሻል በአካባቢው የተወሰኑ ፋሎችን በማስቀመት ሊሰራ የሚችል ይሆናል። ነገር ግን ፣ እነደ መደበኛ ኩኪዎች ሁሉ፣ ለኮፒውተሮ ልዩ መለያ ለማስቀመጥ ሊረዳ ይችላል፣ ይህም የልዩ ባህሪ ዱካን ለመፈለግ ይችላል። እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ( ወይም "ፍላሽ ኩኪዎችን") እና የ Silverlight ትግበራ ማጠራቀሚያ የመሳሰሉትን በአከባቢው የተጋሩ ነገሮችን ያካትታሉ።
በአከባቢው የተጋሩ ነገሮች ወይም "ፍላሽ ኩኪዎች፡፡" አዶቤ ፍላሽ ቴክኖሎጂዎችን የሚጠቀም የድር ጣቢያ በኮመፒውተሮ ላይ ውሂብ ለማከማቸት በአከባቢው የተጋሩ ነገሮችን ወይም "ፍላሽ ኩኪዎችን" ሊጠቀም ችላል። የፍላሽ ኩኪዎችን የማጽዳት ችሎታ እነደየ መቃኛው ልዩነት ለመደበኛ ኩኪዎች በእረስዎ መቃኛ የሚቆጣጠረው ሊሆን ወይም ላይሆን ይችላል። የፍላሽ ኩኪዎችን ለማስተደደር ወይም ለማገድ፣ ወደ http://www.macromedia.com/support/documentation/en/flashplayer/help/settings_manager.html ይሂዱ።
የ Silverlight ትግበራ ማጠራቀሚያ። የMicrosoft Silverlight ቴክኖሎጂዎችን ሚጠቀሙ የድር ገጾች እነደዚሁ የ Silverlight ትግበራ ማጠራቀሚያን በመጠቀም ውሒብ የማከማቸት ችሎታ አላቸው። የዚህ አይነቱን ማከማቻ እንዴት እንደሚያስተዳድሩ ወይም እነደሚያግዱ ለማወቅ፣ Silverlight ን ይጎብኙ።
Microsoft በብቃት ለማከናወን እና የምንችለውን ያህል ለእርስዎ የተመረጡ ምርቶችን፣ አገልግሎቶችን እና ልምዶችን ለማቅረብ ብዙ አይነት መረጃዎችን እንሰበስባለን፡፡
እኛ እረስዎ ሲመዘገቡ ፣ሲገቡ እና ጣቢያዎቻችንን እና አገልግሎቶቻችንን ሲጠቀሙ መረጃ እንሰበስባለን፡፡ በተጨማሪም ከሌላ ካምፓኒዎች መረጃ ልናገኝ እንችላለን፡፡
እኛ የመረብ ቅጽን፣ የኩኪዎችአይነት ቴክኖሎጂዎች፣የድር መስገቢያ እና በእረስዎ ኮምፒውተር ላይ ካሉ ሶፍትዌሮች ወይም ሌሎች መሳሪያዎችን ጨምሮ በተለያየ መንገድ መረጃ እንሰበስባለን፡፡
Microsoft በብቃት ለማከናወን እና የምንችለውን ያህል ለእርስዎ የተመረጡ ምርቶችን፣ አገልግሎቶችን እና ልምዶችን ለማቅረብ ብዙ አይነት መረጃዎችን እንሰበስባለን፡፡ ከእነዚህ ጥቂቱን መረጃ እረስዎ በቀትታ ለእኛ ይሰጡናል፡፡ ጥቂቱን ደግሞ እረስዎ ከእኛ ምርቶች እና አገልግሎቶች ጋር እነዴት እንደሚገናኙ በመመልከት እናገኛለን፡፡ ጥቂቱ ደግሞ ከሌሎች ምንጮች ለምሳሌ በቀጥታ ከምንሰበስበው ዉሂብ ጋር በማደባለቅ የገኛል፡፡ ምነጩ ምንም ይሁን ምን፣ የእርስዎን ሚስጥራዊነት ለመጠበቅ ያንን መረጃ በጥንቃቄ መያዝ ጠቃሚ እንደሆነ እናምናለን፡፡
እኛ የምንሰበስበው:
እኛ ምንሰበስበው:
እንዴት ጣቢያችንን እና አገልግሎቶቻችንን እንደሚጠቀሙ በሚመለከት መረጃ ለመሰብሰብ በርካታ ዘዴዎችን እና ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን፡፡ እነዙህም፡
Microsoft የምንሰጠውን ምረቶችን እና አገልግሎቶችን ለማከናወን፣ ለማሻሻል እና ግላዊ ለማድረግ የምንሰበስበውን መረጀ ይጠቀማል፡፡
እነዲሁም መረጃውን ለምሳሌ ስለ ምዝግቦ እና የደህንነት ማዘመንን በሚመለከት እርሶን ለማስገንዘብ ከህረስዎ ጋር ለመገናኘት እንተቀም ይሆናል፡፡
መረጃውን እረስዎ በማስታወቂያ-ድጋፍ አገልግሎት የተመለከቱትን ማስታወቂ የበለጠ ጠቃሚ ኢነዲሁን ለማድረግ እንጠቀም ይሆናል፡፡
Microsoft የምንሰጠውን ምረቶችን እና አገልግሎቶችን ለማከናወን፣ ለማሻሻል እና ግላዊ ለማድረግ የምንሰበስበውን መረጀ ይጠቀማል፡፡ ከእኛ ጋር በሚኖሮት ግንኙነት የበለጠ ወጥ እና ግላዊ ሆነ ልምድ ለእረስዎ ለማቅረብ በ አንድ Microsoft አገልግሎት የተሰበሰበ መረጃ በሌሎች Microsoft ውስጥ ከተሰበሰቡት መረጃዎች ጋር ይደባለቅ ይሆናል፡፡ ደግሞም ይህንን ከሌላ ካምፓኒ በተገኘ መረጃ ልንተካው እንችላለን፡፡ ለምሳሌ፣ ለእርስዎ መልከዓ ምድር ዙሪያ የተወሰኑ አገልግሎቶችን ለማበጀት ሲባል በ IP አድራሻዎ ላይ መሰረት በማድረግ አጠቃላይ የመልከዓ ምድር ዙሪያን ለመገመት ያስችለን ዘንድ ከሌላ ኩባንያዎች አገልግሎቶችን ልንጠቀም እንችላለን፡፡
እነዲሁም እኛ ለምሳሌ ደንበኝነታችን ማብቃቱን ልናሳዉቆት፣ የደህንነት ማዘመኛ መኖሩን እነዲያውቁት ለማድረግ ወይም መዝግቡን ንቁ ለማድረግ እርምጃ መውሰድ እነደሚያስፈልጎት ለማሳወቅ፣ መረጃውን ልንጠቀምበት ይሆናል፡፡
ምክንያቱም በማስተወቂያ ስለሚደገፉ Microsoftብዙዎቹን የድር ጣቢዎች እና አገልግሎቶችን ከክፍያ ነጻ ቀርባል፡፡ እነዚህ አገልግሎቶች በሰፊው እነዲገኙ ፣ እኛ የምንሰበስበው መረጃ እረስዎ የሚመለከቱት ማስታወቂያ የበለጠ ለእረስዎ ተስማሚ አነዲሆኑ በማድረግ ለማሻሻል እነዲረዳ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡
በዚህ የግል ጉዳይ ደህንነት ላይ ከተገለጸው በቀር፣ ከእረስዎ ስምምነት ውጪ የእረስዎን የግል መረጃ ለሶስተኛ ወገን አሳልፈን አንሰጥም፡፡
የ Microsoft አጋሮችና አከፋፈዮችን ጨምሮ፣ በህግ ሲፈለግ ወይም ለህጋዊ ሂደት መልስ ለመስጠት፤ የማጭበርበር ጉዳይን ለመከላከልና ጥቅማችንን ለማሰጠበቅ፤ ወይም ሂይዎት ለማዳን ሲባል መረጃ መቼ እነደምንለቅ ለዝርዝር መረጃ እባክዎን ሌሎች ጠቃሚ የግል ጉዳይ ደህንነት መረጃዎችን ይመልከቱ፡፡
የግል መረጃን በመጋራት ወይም በመልቀቅ ሁኔታ ላይ ለበለጠ መረጃ እዚህ ላይ ጠቅ ያድረጉ፡፡
ጥቂት የ Microsoft አገልግሎቶች በቀጥታ መስመር ላይ የእርስዎን ግላዊ መረጃ ለማየት እና ለማደት ያስችልዎታል፡፡ የእርስዎ ግላዊ መረጃ በሌሎች እንዳይታይ ለመከላከል፣ በመጀመሪያ እርስዎ መግባት ያስፈልግዎታል፡፡ የግላዊ መረጀዎን ለማግኘት የሚጠቀሙት ዘዴ እርስዎ የተጠቀሙባቸው ጣቢያዎች ወይም አገልግሎቶች ላይ ይመሰረታል፡፡
Microsoft.com - ፕሮፋይሎን የMicrosoft.com ፕሮፋይል ማዕከልን በመጎብኘት በ microsoft.com ላይ ማግኘት እና ማደት ይችላሉ፡፡..
የMicrosoft የክፍያ እና አካውንት አገልግሎቶች -የ Microsoft ክፍያ አካውንት ካለዎት፣ "ግላዊ መረጃን " ወይም "የክፍያ መረጃ " መገናኛዎችን ጠቅ በማድረግበ Microsoft የክፍያ ድረገጽ ጣቢያ ላይ መረጃዎን ማስተካከል ይችላሉ፡፡
Microsoft ግንኙነት - የ Microsoft ግንኙነት የተመዘገቡ ተጠቃሚ ከሆኑ፣ በ Microsoft ግንኙነት ድረገጽ ላይ የግንኙነት የግል ማህደሮን ያስተዳድሩ የሚለውን ጠቅ በማድረግ ግላዊ መረጃዎን ማግኘት እና ማስተካከል ይችላሉ፡፡
Windows Live -የ Windows Live አገልግሎቶችን የሚጠቀሙ ከሆነ፣ የመገለጫ መረጃዎን ማዘመን፣ የይለፍ ቃልዎን መለወጥ፣ ከምስክር ወረቀትዎ ጋር ተያያዥነት ያለውን ልዩ መታወቂያ መለወጥ፣ ወይም የተወሰኑ መለያዎችን Windows Live የምዝግብ አገልግሎቶችን በመጎብኘት መዝጋት ይችላሉ፡፡..
Windows Live የህዝብ መገለጫ - በ Windows Live ላይ የህዝብ መገለጫ ከፈጠሩ ፣ ወደ እርስዎ መገለጫ በመሄድ በህዝብ መገለጫዎ ውስጥ ያለውን መረጃ አርትዕ ማድረግ ወይም መሰረዝ ይችላሉ፡፡.
ማስታወቂያን ፈልግ - Iበ Microsoft ማስታወቂያ አማካኝነት ማስታወቂያን ፈልግ ከገዙ፣ በ Microsoft የማስታወቂያ ማዕከል የድር ገጽላይ ግላዊ መረጃዎን መከለስ እና አርትዕ ማድረግ ይችላሉ፡፡.
Microsoft አጋር ፕሮግራሞች - በ Microsoft አጋር ፕሮግራሞች ላይ ከተመዘገቡ፣ በአጋር ፕሮግራም ድረገጽ ላይ መለያዎን ያስተዳድሩ የሚለውን ጠቅ በማድረግ መገለጫዎን መከለስ እና ማስተካከል ይችላሉ፡፡
Xbox - Xbox LIVE ወይም Xbox.com ተጠቃሚ ከሆኑ፣ የእኔ Xboxን በ Xbox 360 ምቾት ላይ ወይም በ My Xbox ድረገጽ ላይ በማግኘት ግላዊ መረጃዎን የክፍያ እና የመለያ መረጃን፣ የግላዊነት ቅንጅቶችን፣ የመስመር ላይ ደህንነት እና የውሂብ መጋራት አማራጮችን ማየት ወይም አርትዕ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ለመለያ መረጃ የእኔ Xbox፣ መለያዎችን ይምረጡ፡፡ ለሌላ ግላዊ መረጃ ቅንጅቶች፣ የእኔ Xbox መገለጫን ይምረጡ፣ እና የቀጥታ መስመር ላይ ደህንነት ቅንጅቶችን ይምረጡ፡፡
Zune -የ Zune መለያ ወይም የ Zune የደንበኝነት ማለፊያ ካለዎ፣ በ Zune.net (ላይ ግላዊ መረጃዎን ማየት እና ማስተካከል ይችላሉ (ይግቡ፣ የ Zune ስያሜ ያግኙ ከዚያም የእኔ መለያ ወይም በ Zune ሶፍትዌር አማካኝነት ያግኙ (ይግቡ፣ የ Zune ስያሜ ያግኙ ከዚያም Zune.net መገለጫን ይምረጡ፡፡)"
እንደ አጋጣሚ ከዚህ በላይ ባሉት መገናኛዎች አማካኝነት በ Microsoft ጣቢያዎች ወይም አገልግሎቶች የተሰበሰበ ግላዊ ዳታን ማግኘት ካልቻሉ፣ እነኝህ ጣቢያዎች እና አገልግሎቶች ዳታዎን እንዲያገኙ አማራጭ መንገዶችን ያቀርቡልዎታል፡፡ የድር ቅፅንበመጠቀም Microsoftnን ማግኘት ይችላሉ፡፡ . የግል መረጃዎን ለማግኘት እና ለመሰረዝ ጥያቄዎች ካቀረቡ በ 30 ቀናት ውስጥ ምለሽ እንሰጣለን.
የ Microsoft ጣቢያ ወይም አገልግሎት የዕድሜ መረጃ ሲሰበስብ፣ እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች ያሉ ልጆችን ያግዳል ወይም ከቤተሰብና ከሞግዚት ልጃቸው ለመጠቀም ከመቻሉ በፊት ስምምነታቸውን ማግኛት ይኖርብናል፡፡
ስምምነት ሲገኝ፣ ከሌሎች ተጠቃሚዎች ጋር መገናኘትን ጨምሮ የልጁ ምዝግብ እንደማንኛውም ምዝግብ በበቂ ሁኔታ ሊስተናገድ የችላል፡፡
በዚህ ሚስጥራዊ መጠበቂያ ወላጆች ስምምነታቸውን መቀየር ወይም ተቃውሞ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
የ Microsoft ጣቢያ ወይም አገልግሎት የዕድሜ መረጃ ሲሰበስብ፣ እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች ያሉ ልጆችን ያግዳል ወይም ከቤተሰብና ከሞግዚት ልጃቸው ለመጠቀም ከመቻሉ በፊት ስምምነታቸውን ማግኛት ይኖርብናል፡፡ ከ13 አመት በታች የሆኑ ልጆችን አገልግሎቱን ለማቅረብ ተገቢ ከሆነው በላይ መረጃ ሆን ብለን እንዲያቀርቡ አንጠይቅም፡፡
ስምምነት ሲገኝ፣ ከሌሎች ተጠቃሚዎች ጋር መገናኘትን ጨምሮ የልጁ ምዝግብ እንደማንኛውም ምዝግብ በበቂ ሁኔታ ሊስተናገድ የችላል፡፡ ልጁ ወይም ልጅቷ እንደ ኢሜይል፣ ፈጣን መልዕክት፣ የቀጥታ መስመር መልዕክት ቦርዶች የአገልግሎት ግንኙነቶችን ማግኘትና ከሁሉም ዕድሜ ደረጃ ተጠቃሚዎች ጋር በነጻ መገኛኘት ይችሉ ይሆናል፡፡
ወላጆች ቀድሞ የተሰጠውን ስምምነት ምርጫ ሊቀይሩ ወይም ሊስርዙ፣ እና ሊከልሱ፣ አርትኢ ሊያደርጉ ወይም የልጆቻቸው የግል መረጃዎች እንዲስረዙ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፣በ Windows Live ላይ፣ ወላጆች ምዝግባቸውን መጎብኘትና ‹‹የወላጅ ፍቃድ›› ላይ ጠቅ ማድረግ ይችላሉ፡፡.
በ Microsoft ጣቢዎች እና አገልግሎቶች ላይ አብዛኛዎቹ የቀጥታ መስመር ማስታወቂዎች በ Microsoft ማስታወቂያ የሚታዩ ናቸው፡፡ ለእርስዎ የመስመር ላይ ማስታወቂያዎችን በምናሳይበት ጊዜ በእያንዳንዱ ጊዜ ለእርሶ ማስታወቂያዎችን ስናሳይ ኮምፒዩተሮን ለመለየት የሚረዱን አንድ ወይም ከዚያ በላይኩኪዎችን እናስቀምጣለን፡፡ ትርፍ ሰዓት፣ የበለጠ ጠቃሚ ማስታወቂያዎችን ለማቅረብ የማስታወቂያ አገልግሎት ከምናቀርብበትና እና መረጃ ከምንጠቀምበት ጣቢዎች መረጃ እንሰበስብ ይሆናል፡፡
ከ Microsoft ማስታወቂያ የሚደርሶወን የተነጣጠሩ ማስታወቂያዎችን የማግለል ገጻችንን በመጎበኘት እንዚህን ማስተወቂያዎቸን መግለል ይችላሉ፡፡.
ብዙዎቹ የእኛ የድር ጣቢያዎች እና የቀጥታ መስመር አገልግሎቶች በማስታወቂያ የተደገፉ ናቸው፡፡
በ Microsoft ጣቢያዎች ላይ ያሉ አብዛኞቹ የቀጥታ መስመር ማስታወቂያዎች በ Microsoft ማስታወቂያ የሚታዩ ናቸው፡፡ ለእርስዎ የመስመር ላይ ማስታወቂያዎችን በምናሳይበት ጊዜ በእያንዳንዱ ጊዜ ለእርሶ ማስታወቂያዎችን ስናሳይ ኮምፒዩተሮን ለመለየት የሚረዱን አንድ ወይም ከዚያ በላይ ኩኪዎችን እናስቀምጣለን፡፡ ማስታወቂያዎችን በራሳችን ድር ጣቢያዎች እንዲሁም የማስተዋወቅ እና የማሳተም አጋሮቻችን ላይ ስለምናገልግል፣ እርሶ ወይም ሌሎች ኮምፒዩተርዎን የሚጠቀሙ ሰዎች በተወሰነ ጊዜ ስለጎበኟቸው ወይም ስለተመለከቷቸው የገጾች አይነት፣ ይዘት እና ማስታወቂያዎች መረጃዎች ማጠናከር እንችላለን፡፡ ይህ መረጃ ለብዙ አለማዎች ይውላል፣ ለምሳሌ፣ ተመሳሳይ ማስታወቂያዎችን በተደጋጋሚ እንዳያዩ ለማድረግ እንድንሞክር ይረዳናል፡፡ በተጫመሪ ይህንን መረጃ የእርሶ ፍላጎት ሊሆኑ ይችላሉ ያልናቸውን የተነጣጠሩ ማስታወቂያዎችን መምረጥ እና ማሳየት ለመርዳት እንጠቀምበታለን፡፡
ከ Microsoft ማስታወቂያ የሚደርሶወን የተነጣጠሩ ማስታወቂያዎችን የማግለል ገጻችንን በመጎበኘት እንዚህን ማስተወቂያዎቸን መግለል ይችላሉ፡፡. Microsoft ማስታወቂያ እንዴት መረጃ እንደሚሰበስብ እና እንደሚጠቀም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ Microsoft ማስተወቂያ ግላዊነት ድጋፍ ይመልከቱ፡፡.
በተጨማሪ ሶስተኛ ወገን ማስታወቂያ ድርጅቶች፣ ሌሎች የማስታወቂያ አውታረ መረቦችን ጨምሮ፣ ማስታወቂያዎችን በእኛ ጣቢያዎች ላይ እንዲያሳዩ እንፈቅዳለን፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ እንዚህ ሶስተኛ አካላት በኮምፒዩተርዎ ላይ ኩኪዎች ሊያስቀምጡ ይቻላሉ፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች በአሁኑ ሰአት ይከተታሉ፣ ነገር ግን ለሚከተሉት የተወሰኑ አይደሉም፡ 24/7 Real Media, adblade, AdConion, AdFusion, Advertising.com, AppNexus, Bane Media, Brand.net, CasaleMedia, Collective Media, InMobi, Interclick, Jumptap, Millennial Media, nugg.adAG, Mobclix, Mojiva, SpecificMedia, Tribal Fusion, ValueClick, Where.com, Yahoo!, YuMe, Zumobi. እነዚህ ኩባንያዎች በኩኪዎቻቸው ላይ የተመሰረቱ ማስታወቂያዎቸን ለማግለያ ዘዴዎች ሊያቀብሎት ይችላሉ፡፡ ከላይ የሚገኘው የኩባንያዎች ስም ላይ ጠቅ በማድረግ እና ወደ እያንዳንዱ ኩባንያ ድር ጣቢያዎች መገናኛውን በመከተል ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይቻላሉ፡፡ እያንዳዳቸው ከተሳታፊ ኩባኒያዎች ውጪ የሚያነጣጥሩ ማስተወቂያዎች የሚያስወጣ ቀላል መንገድ የሚያቀርቡ አብዛኛዎቹ የአውታረ መረብ ማስታወቂያ ማነሳሺያ ወይም የ አሃዛዊ ማስታወቂያ አሊያነስአባል ናቸው፣
የመረጃ ልውውጥ አማራጮች የሚቀበሉት ኢ-ሜይል ውስጥ ያሉትን የተወሰኑ ትዕዛዛት በመከተል ከ Microsoft ጣቢያዎች እና አገልግሎቶች ወደፊት የሚመጡ የማስታወቂያ ኢ-ሜይሎች እንዳይደርስዎት ማድረግ ይችላሉ። ተከታዩ አገልግሎት ላይ መሰረት በማድረግ፣ የሚከተሉተን ገጾች በመጎብኘት እና ወደ ገጾቹ በመግባት ከተወሰኑ የ Microsoft ጣቢያዎች ወይም አገልግሎቶች የሚመጡ የማስታወቂያ ኢ-ሜይልን፣ የስልክ ጥሪዎችን፣ እና የፓሰታ መልዕክትን ቀድመው ሊመርጡ የሚችሉበት አማራጭ ሊኖርዎ ይችላል።
የማስጣወቂያ መልዕክቶችን ከእኛ ከተቀበሉና ወደፊት መቀበሉን ማቆም ካፈለጉ፣ በመልእክቱ ውስጥ የሚገኛውን መመሪያ በመከተል ሊፈጽሙት ይችላሉ።
ተከታዩ አገልግሎት ላይ መሰረት በማድረግ፣ የሚከተሉተን ገጾች በመጎብኘት እና ወደ ገጾቹ በመግባት ከተወሰኑ የ Microsoft ጣቢያዎች ወይም አገልግሎቶች የሚመጡ የማስታወቂያ ኢ-ሜይልን፣ የስልክ ጥሪዎችን፣ እና የፓሰታ መልዕክትን ቀድመው ሊመርጡ የሚችሉበት አማራጭ ሊኖርዎ ይችላል፡
እነኝህ አማራጮች በቀጥታ መስር ላይ ያሉ ማስታወቂያዎች ማሳያ ላይ በስራ ላይ አይውሉም፡ እባክዎን “የማስታወቂያ ማሳያ (ማግለል)” ይህንን ጉዳይ በተመለከተ መረጃ ለማግኛት ወደ ክፍሉ ያምሩ። አገልግሎቱን ካልሰረዙ በቀር በየጊዜው እርስዎ ሊቀበሉ ከሚችሏቸው የተወሰኑ የ Microsoft አገልግሎቶች ተብለው ከሚቆጠሩትን የመደበኛ አገልግሎት የመረጃ ልውውጥ መቀበዎች ላይ ተግባራዊ አይደረግም።
በመገኛ ስፍራ ላይ የተመረኮዘ አገልግሎት ወይም ባህሪ ሲጠቀሙ፣ ሊገኝ የሚችለው የሴል ማማ ውሂብ፣ የ Wi-Fi ውሂብ እና Global Position System (GPS) ውሂብ ወደ Microsoft ሊላክ ይችላል። Microsoft የመገኛ ስፍራን መረጃ እርስዎ የጠየቁትን አገልግሎት ለመስጠት፣ ተሞክሮዎን ለግል ብጁ ለማድረግ እና የ Microsoft ምርቶች እና አገልግሎቶችን ለማሻሻል ይጠቀምበታል።
አንዳንድ የተወሰኑ አገልግሎቶች የመገኛ ስፍራ መረጃ ወደ Microsoft ሲላክ ወይም ለሌሎች እንዲያገኙት ሲደረግ እርስዎ መቆጣጠር እንዲችሉ ይፈቅዱሎት ይሆናል። በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ የመገኛ ስፍራ መረጃ ለአገልግሎቱ በጣም አስፈላጊ ሊሆን እና የመገኛ ስፍራ መረጃዎን መላክ ለማስቆም የባህሪው መራገፍ ሊያስፈልገው ወይም አገልግሎቱን ማቋረጥ ሊያስፈልገው ይችል ይሆናል። የመገኛ ስፍራን ባህሪያት እንዴት ማጥፋት እንደሚቻል መረጃ ለማግኘት ከመሳሪያዎ ጋር አብሮ የመጡትን ሰነዶች ይመልከቱ።
የድጋፍ ውሂብ እርስዎ የድጋፍ ጥያቄ ሲያቀርቡ ወይም ስለሃርድ ዌር፣ ሶፍትዌር መረጃን እንዲሁም ከድጋፍ አጋጣሚው ጋር የተዛመዱ የሚከተሉትን የሚያጠቃልሉ ሌሎች ዝርዝሮች ጨምሮ ጨምሮ የራስ ሰር መላ ፍለጋ ሲያስኬዱ የምንሰበስበው መረጃ ነው፦ እውቂያ ወይም የማረጋገጫ መረጃ፣ የውይይት ክፍለ ጊዜን ለግል ማበጀት፣ የማሽኑን ሁኔታና ችግሩ የተነሳበትን መተግበሪያ የተመለከተ መረጃ እንዲሁም ስለ ሶፍትዌር መጫን እና ሃርድዌር ማዋቀርን የተመለከቱ የምርመራ ወቅት፣ የስርአት እና የምዝገባ ውሂብ እና ስህተት መከታተያ ፋይሎች። የድጋፍ ውሂብን በዚህ የግላዊነት መግለጫ ላይ በተገለጸው መሰረት የምንጠቀመው ሲሆን በተጨማሪም የድጋፍ ክስተቶችዎን ለመፍታት እና ለስልጠና አላማዎች ጥቅም ላይ እናውለዋለን።
ድጋፍ በስልክ፣ በኢሜይል ወይ በመስመር ላይ ውይይት ሊቀርብ ይችላል። በርስዎ ፈቃድ ላይ በመመስረት ዴስክቶፕዎን በጊዜያዊነት ለመቃኘት የርቀት መዳረሻውን (ርመ) ልንጠቀም እንችላለን። የስልክ ንግግሮች፣ የመስመር ላይ የውይይት ክፍለ ጊዜዎች ወይም ከድጋፍ ባለሞያዎች ያሉ የሩቅ መዳረሻ ክፍለ ጊዜዎች ሊቀዱ እና/ወይም ቁጥጥር ስር ሊሆኑ ይችላሉ። ለሩቅ መቆጣጠሪያው ቅጂውን ከክፍለ ጊዜዎ በኋላ ሊደርሱት ይችላሉ። ለመስመር ላይ ውይይት ወይም ለሩቅ መዳረሻ ክፍለ ጊዜን በመረጡት ጊዜ ማቆም ይችላሉ።
የድጋፍ ክስተትን ተከትሎ ተሞክሮዎን እና ቅናሾችን የተመለከቱ ጥናቶችን ልንልክልዎ እንችላለን። ድጋፍን በማግኘት ወይም በኢሜይል ግርጌ በመጠቀም በMicrosoft ከሚቀርቡ ሌሎች የግንኙነት መልእክቶች ጋር ሳይገናኝ በተናጠል ከድጋፍ ጥናቶች መርጠው መውጣት ይችላሉ።
በድጋፍ አገልግሎቶቻችን አማካኝነት የተሰበሰቡ የግል መረጃዎን ለመገምገም እና አርትእ ለማድረግ እባክዎ በ ድር ቅፃችን ያግኙን።
አንዳንድ የንግድ ደምበኞች የላቁ የድጋፍ ቅናሾችን (ለምሳሌ ዋናን የመሳሰሉ) ሊገዙ ይችላሉ። እነዚህ ቅናሾች በራሳቸው የእውቂያ ደንቦች እና ማስታወቂያዎች ይሸፈናሉ።
የክፍያ ውሂብ በመስመር ላይ ግብይት ሲፈጽሙ የሚሰጡት መረጃ ነው። ይህ የእርስዎን የክፍያ ስልት ቁጥር (ለምሳሌ፥ ክሬዴት ካርድ፣ PayPal)፣ የእርስዎን ስም እና ክፍያ መጠየቂያ አድራሻ፣ እንዲሁም ከክፍያ ስልትዎ ጋር የተቆራኘ የመድህን ኮድን ሊያካትት ይችል ይሆናል (ለምሳሌ፥ CSV ወይም CVV)። ይህ ክፍል የእርስዎ የክፍያ ስልት መረጃ እንዴት እንደሚሰበሰብ እና እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል።
የክፍያ ስልት ግብይትዎን ለማጠናቀቅ እና የማጭበርበር ወንጀልን ለይቶ ለማወቅ እና ለመከላከል ጥቅም ላይ ይውላል። ይህን በመደገፍ፣ Microsoft ከባንኮች እና ከሌሎች በክፍያ የሚፈጸሙ ግብይቶችን ከሚያከናውኑ ተቋማት ጋር ወይም ከሌሎች የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር እንዲሁም የማጭበርበር ወንጀልን ለመከላከል እና የክሬዲት አደጋ ላይ የመውደቅ ዕድልን ለመቀንስ የእርስዎን የክፍያ ውሂብ ሊያጋራው ይችላል።
በየእርስዎ Microsoft ወይም የድርጅት መለያ ተመዝግበው ገብተው እያሉ የክፍያ ውሂብዎን ሲሰጡ ወደፊት የሚያደርጉትን ግብይት ለማጠናቀቅ እንዲያግዝ ያንን ውሂብ እናስቀምጠዋለን።
ወደ https://commerce.microsoft.comተመዝግበው በመግባት ከእርስዎ የ Microsoft መለያ ጋር የተቆራኘውን የክፍያ ስልት መረጃ ሊያዘምኑት ወይም ሊያስወግዱት ይችላሉ። ከእርስዎ ድርጅት ጋር የተቆራኘውን የክፍያ ስልት መረጃ የደንበኛ ድጋፍ ን በማነጋገር ሊያስወግዱት ይችላሉ። ሆኖም ግን መለያዎን ከዘጉ በኋላ ወይም የክፍያ ስልትዎን ካስወገዱ በኋላ፣ Microsoft አሁን በመከናወን ያለ ግብይትዎ እስከሚጠናቀቅ አስፈላጊ እስከሚሆንበት ጊዜ ድረስ፣ Microsoft ያሉበትን ሕጋዊ እና ሪፖርት የማድረግ ግዴታዎችን እስከሚወጣ ድረስ እንዲሁም የማጭበርበር ወንጀልን ለይቶ ለማወቅ እና ለመከላከል ሲባል የክፍያ ስልትዎን ውሂብ ሳይጥል ሊያስቀምጠው ይችላል።
ወደ Microsoft ምርቶች የድር ጣቢያዎችና አገልግሎቶች እነዲሁም ወደ ተመረጡ የ Microsoft አጋሮች ለመግባት የሚፈቅድሎት አገልግሎት ነው፡፡ የ Microsoft ምዝግብ ሲፈጥሩ ፣ የተወሰኑ መረጃዎችን እነዲሰጡ ልንጠይቆት እንችላለን፡፡ የ Microsoft ምዝግቦን ተጠቅመው ወደ ጣቢያ ወይም ምርት ሊገቡ ሲሉ፣ ከማይገባ ምዝግብ አጠቃቀም እረስዎን ለመከላከል፣ እነዲሁም የ Microsoft ምዝግ አገልግሎት ብቃትን እና ደህንነት ለማስጠበቅ ጣቢያውን ወይም አገልግሎቱን ወክለን ማንነቶን ለመለየት የተወሰኑ መረጃዎችን እንሰበስባለን፡፡ ከ Microsoft ምዝግቦ ጋር ደግሞ የተወሰኑ መረጃዎችን እረስዎ ወደገቡበት ጣቢያ ወይም አገልግሎት እንልካለን፡፡
የMicrosoft ምዝግብን እንዴት እነደምንከፍት እና ከ Microsoft ምዝግብ ጋር የሚገናኙ መረጃዎችን እነዴት እነደምንሰበስብ እና እነደምንጠቀም ጨምሮ ስለ Microsoft ምዝግብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎን በተጨማሪ መማር የሚለውነ ጠቅ ድርጉ፡፡
የ Microsoft ምዝግብ (በቀድሞው Windows Live ID እና Microsoft ፓስፖርት የሚባለው) ወደ Microsoft ምርቶች የድር ጣቢያዎችና አገልግሎቶች እነዲሁም ወደ ተመረጡ የ Microsoft አጋሮች ለመግባት የሚፈቅድሎት አገልግሎት ነው፡፡ ይህም የሚከተሉትን ምርቶች፣ የድር ጣቢያዎች እና አገልግሎቶችን የመሳሰሉትነ ያካትታል፡
የ Microsoft ምዝግብን መፍጠር፡፡
ከዚህ ቀጥሎ የኢ-ሜይል አድሻ ፣ የይለፍ ቃል እና እነደ አማራጭ የኢ-ሜይል አድራሻ ፣ የስልክ ቁጥር እና ጥያቄ እና የሚስጢር መልስ የመሳሰሉትን ሌሎች ‹‹ የምዝግብ ማረጋገጫዎች››ን በማቅረብ የ Microsoft ምዝግብ መፍጠር ይችላሉ፡፡ እኛ የእረስዎን ‹‹ የምዝግብ ማረጋገጫዎች››ን ለደህንነት ጉዳይ ብቻ - ለምሳሌ፣ የ Microsoft ምዝግቦን ለማግኘት ሳይችሉ ሲቀሩ እና እገዛ ሲፈልጉ፣ ወይም ከ Microsoft ምዝግቦ ጋር የተገናኙ የኢ-ሜይል አድራሻ ማግነት ሳይችሉ ሲቀሩ የይለፍ ቃሎን እንደገና ለማስገባት ሲሉ እንጠቀማለን፡፡ አንዳንድ አገልግሎቶች ተጨማሪ ደህንነት ሊጠይቁ ይችላሉ፣ እናም በዚህ ጉዳይ ላይ፣ ተጨማሪ የደህንነት አዝራር እንዲፈጥሩ ሊጠየቁ ይቻለሉ፡፡ ለእኛ Microsoft ምዝግብ ለመመዝገብ የተጠቀሙበት የኢ-ሜይል አድራሻ እና የይለፍ ቃል በእኛ መረብ እነደማረጋገጫነት የሚጠቀሙበት የእረስዎ ‹‹ መለያዎች›› ናቸው፡፡ በመጨረሻ፣ አሳማኝ መታወቂያዎን እና ተያያዥ መረጃዎችን ለመለየት የሚጠቅሙ የ 64-bit ልዩ መታወቂያ ቁጥር ለአሳማኝ መታወቂያዎ ይስየማል፡፡
የ Microsoft ምዝግብ ሲፈጥሩ፣ እነደዚሁ የሚከተሉትን ግላዊ መረጃዎች እነዲያስገቡ እንጠይቆጣለን፡፡ ጾታ፤ ሀገር፤ የትውልድ ቀን፤ እና የፖሰታ ኮድ፡፡ የአካባቢው ህግ በሚጠይቀው መሰረት፣ ህጻናት Microsoft ምዝግብን ለመጠቀም ከቤተሰብ ተገቢውን ስምምነት ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ የትውልድ ቀንን እንጠቀም ይሆናል፡፡ በተጨማሪም፣ ይህ የግል መረጃ ስለ ምርቶች እና አገልግሎቶች ጠቃሚ ነው ብለው የሚፈልጉትን ግለሰብ ተኮር ማስታወቂያዎችን ለማቅረብ በቀጥታ መስመር የማስታወቂያ ሲስተማችን ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፣ነገርግን የእኛ የማስጣወቂያ ሲስተም የእረስዎን ስም እና የመገኛ መረጃ በፍጹም ማግኘት አይችልም፡፡ በሌላ አባባል የእኛ የማስታወቂያ ሲስተም እረስዎን በግል እና በቀጥታ መለየት የሚየስችሉ ምንም ዓይነት መረጃ (እንደ ስም፣ ኢ-ሜል አድራሻ እና የስልክ ቁጥር የመሳሰሉትን) ማግኘት ወይም መጠቀም አይችልም፡፡ ግላዊ ማስታወቂያዎችን ለማግኘት ካለፈለጉ፣ይህንን ጣቢያ በመጎብኘት በ Microsoft ምዝግቦ ላይ ምርጫዎን ይመዘግቡ ይሆናል፣በመሆኑም በ Microsoft ምዝግቦ ወደ የድር ገጽ በገቡ ጊዜ፣ የእኛ የማስታወቂያ ሲስተም የእረስዎን ግላዊ ማስታወቂ አይሰጦትም፡፡ Microsoft ማስታወቂያ እንዴት መረጃ እንደሚሰበስብ እና እንደሚጠቀም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ Microsoft ማስተወቂያ ግላዊነት ድጋፍ ይመልከቱ፡፡..
ለ Microsoft ምዝግብ ሲያመለክቱ በ Microsoft የሚቀርብሎትን የኢ-ሜይል አድራሻ ( እነደ live.com, hotmail.com, አሊያም msn.com በማለት የሚጨርሱትን) ወይም በሌላ ሶስተኛ ወገን በሚቀርብሎት የኢ-ሜይል አድራሻ (እንደ gmail.com ወይም yahoo.com ብለው በሚጨርሱት) መጠቀም ይችላሉ፡፡
የ Microsoft ምዝግቦን ሲፈጥሩ፣ እረስዎ ከ Microsoft ምዝግብ ጋር የተገናኘ የኢሜይል አድራሻ ባለቤት መሆኖን እነዲያረጋግጡ የሚጠይቅ ኢሜይል እንልከሎታለን፡፡ ይህ ሂደት የኢ-ሜየል አድራሻ ዋጋ ያለው መሆኑን ለማረጋገገጥ እና የኢ-ሜይል አድራሻዎች ያለባለቤቱ ፈቃድ ጥቅም ላይ እንዳይውል ለመከላከል የተነደፈ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ፣ ከእረስዎ Microsoft ምርቶች እና አገልግሎቶች ጋር የተያያዙ ግንኑነቶችን ለመላክ ያንን ኢ-ሜይል እንጠቀም ሆናል፤ ደግሞም፣ በአካባቢው ህግ በተፈቀደው መሰረት ስለ Microsoft ምርቶች እና አገልግሎቶች በተመለከተ የማስተዋወቂያ ኢ-ሜይል እንልክ ይሆናል፡፡ ለ የማስተዋወቂያ ግንኙነቶን ማስተዳደርን በሚመለከት ለመረጃ ፣ እባክዎን ግንኙነቶች የሚለውንይጎብኙ፡፡
ለ Microsoft ምዝግብ ለማመልከት ሞክረው ሌላ ሰው ቀድሞ በእረስዎ የኢሜይል አድራሻ እነደ ተጠቃሚ መለያ መታወቂያ ፈጥሮ ከሆነ እናን በማግኘት ሌለኛው ሰው ሌላ አዲስ የተጠቃሚ ስም እንዲያሻሽል በመየቅ እረስዎ የእርሰዎን መለያ ለመፍጠር የኢ-ሜይልድራሻዎን መጠቀሙ ይሆናል፡፡
በእረስዎ Microsoft ምዝግብ ወደ ሶፍትዌር፣ ጣቢያዎች ወይም አገልግሎቶች መግባት፡፡
የ Microsoft ምዝግቦን በመጠቀም ወደ ጣቢያ እና አገልግሎት ሲገቡ፣ ጣቢያውን እና አገልገሎቱን በመተካት ማንነቶን ለማረጋገጥና እረስዎን አግባብ ካለሆነ የምዝግብ አጠቃቀም ለመከላከል ፣ እንዲሁም የ Microsoft ምዝግብ አገልግትን ብቃትና ደህንነት ለመጠበቅ፣ የተወሰኑ መረጃዎችን እንሰበስባለን፡፡ ለምሳሌ፣ ሲገቡ፣ የ Microsoft ምዝግብ አገልግሎት የእርስዎን መለያ እና ሌሎች መረጃዎችን እንደ 64-bit ቢት ልዩ የመታወቂያ ቁጥር ለእረስዎ መለያ የተሰጠ፣የእረስዎን IP አድራሻ ፣ የእረስዎን መረብ መቃኛ እትም እና ጊዜ እነዲሁም ቀን ፣ ተቀብሎ ይገፍታል፡፡ በተቸማሪም፣ በኮምፒውተሮ ላይ ወደ ተጫነ መሳሪያ ወይም ሶፍትዌር ለመግባት የ Microsoft ምዝግብን የሚጠቀሙ ከሆነ፣ የተሰባጠረ ልዩ ID ለመሳሪያው የሰጠዋል፤ በ Microsoft ምዝግብዎ ወደ ጣቢያ ወይም አገልግሎት ወዲያው እንደገቡ ይህ ስብጥር ልዩ ID የእረስዎ መለያ ተደርጎ ለ Microsoft ምዝግብ አገልግሎት ይላካል፡፡ የ Microsoft ምዝግብ አገልግሎት እረስዎ ወደገቡበት ጣቢያ ወይም አገልግሎት የሚከተለውን መረጃ ይልካል ፡ ጣቢያው ወየም አገልገሎቱ እረስዎ መጀመሪያ ከገቡበት ክፍለጊዜ ወደ ቀጣዩ ሲሸጋገሩ ተመሳሳይ ሰው መሆኖን ለመፍቀድ ልዩ ID ፣ የእትም ቁጥር ለእርሰዎ ምዝግብ የሚሰጥ (የመግቢያ መረጃዎን በቀየሩ ቁጥር አዲስ ቁጥር ይሰጣል)፤ የእርስዎ ኢ-ሜይል አድራሻ ተረጋግጦ እነደሆነ፤ እነዲሁም የእረስዎ ምዝግብ የቦዘነ እነዲሆን ተደርጎ እነደሆነ፡፡
እረስዎ በ የMicrosoft ምዝግብ እነዲገቡ የሚፈቅዱ የተወሰነ ሶስተኛ ወገን ጣቢያ ወይም አገልግሎቶች አገልገሎቶቻቸውን ለእርስዎ ለማቅረብ የእረስዎን የኢ-ሜይል አድራሻ ይጠይቃሉ፡፡ በዚህ ሁኔታዎች፣ሲገቡ፣ Microsoft ለጣቢያው ወይም ለአገልግሎቱ የኢሜል ድራሻዎን ያቀርባል ነገር ግን የይለፍ ቃሎን አይሰጥም፡፡ ነገርግን፣ በሳይቱ ወይም አገልግሎቱ የእርስዎን መለያ የፈጠሩ ከሆነ፤ የይለፍ ቃሎን ለመቀየር ከመርዳት ወይም ሌሎች የድጋፍ አገልግሎቶችን ከማቅረብ ጋር በተያያዘ የተወሰነ ገደብ ሊኖረው ይችላል፡፡
የእረስዎን ምዝግብ እነደ ትምህርት ቤት፣ ቢዝነስ፣ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ፣ ቁጥጥር ያለበት ቡድን አስተዳዳሪ ከመሳሰሉት ከሌላ ሶስተኛ ወገን ከተቀበሉ፣ ያ ሶስተኛ ወጋን የይለፍ ቀሎን የመለወጥ ችሎታ፣ የእርስዎን የምዝግብ አጠቃቀም ወይም የመገለጫ ውሂብ፣ በ መዝግቦ የተቀመጠ መረረጃዎን የማነበብ፣ እና ምዝግቦን የመደበቅ ወይም የመሰረዝ የመሳሰሉትን ጨምሮ በምዝግቦ ላይ መብት ሊኖረው ይችላል፡፡ በእነዚህ ሁኔታዎች ዉስጥ፣ ለ Microsoft አገልግሎትስምምነትና ከዚ ሶስተኛ ወገን ለሚቀርብ ማንኛውም ተጨማሪ የአጠቃቀም ግዴታ ተገዢ ይሆናሉ፡፡ እርስዎ የተገደበ ጎራ አስተዳዳሪ ከሆኑና ተጠቃሚዎ የ Microsoft ምዝግብ ያገኙ ከሆነ፣ በእነዚያ ምዝግቦች ውስጥለሚከናወ መንኛቸውም ነገሮች እረስዎ ኃላፊነት አለብዎት፡፡
ልብ ያድርጉ የ Windows Live መታወቂያን አገልግሎት የሚጠቀሙ ጣቢያዎች እና አገልግሎቶች በግላዊነት መግልጫቸው ላይ በገለጹት መሰረት የሰጧቸውን የኢሜይል አድራሻዎን ወይም ሌሎች ግላዊ መረጃዎችን ሊጠቀሙባቸው ወይም ለሌሎች ሊያጋሯቸው ይችላሉ፡፡ ነገርግነ፣ ከሶስተኛ ወገን ጋር ብቻ ከ Microsoft ምዝግብ አገልግሎት የተሰጣቸውን ልዩ ID አገልግሎቶችን ለመጠቀም ወይም ትራንዛክሽን እረስዎ ሊጠየቁ የሚችሉትን እነሱ ሊጋሩ ይችላሉ፡፡ ሁሉም የ Windows Live የሚጠቀሙ ጣቢያዎች እና አገልግሎቶች የተለጠፈ የግላዊነት መግለጫ እንዲኖራቸው ይጠየቃል፡፡ ነገር ግን እኛ የግላዊነት ልምዳቸውን አንቆጣጠረም ወይም አንከታተልም፣ የግላዊነት ልምዶቻቸው የተለያዩም ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ጣቢያ ወይም አገልግሎት የሚሰበስበውን መረጃ እንዴት እንደሚጠቀምብት ለመለየት እያንዳንዱ የሚገቡበትን ጣቢያ የግላዊነት መግለጫ በጥንቃቄ ይመርምሩ፡፡
ወደመለያ አገልግሎት በመሄድ የግል መረጃዎ ጋር መድረስ ይችላሉ፡፡. የ Windows Live መታወቂያዎ የሰፖንስር የተደረገ ጎራ ንብረት ካልሆነ የተጠቃሚ ስምዎን መቀየር ይችላሉ፡፡ የይለፍ ቃልዎን፣ ተለዋጭ ኢ-ሜይል አድራሻዎን፣ እና ጥያቄ እና ሚስጥራዊ መልሶን ሁልጊዜም መቀየር ይችላሉ፡፡ ወደ ምዝግብ ከዚያም ‹‹ምዝግቦን ይዝጉ›› ወደሚለው በመሄድ የ Microsoft ምዝግቦን ሊዘጉ ይችላሉ፡፡ መለያዎ ስፖንሰር በተደገ ጎራ ውስጥ ከሆነ ከላይ እንደተጠቀሰው መለያዎትን ለመዝጋት የተለየ ሂደት ያስፈልጋል፡፡ እባክዎን ይገንዘቡ እረስዎ የ MSN ወይም የ Windows Live ተጠቃሚ ከሆኑ፣ ወደ እነዚያ ጣቢያዎች ምዝግብ እንደገና ሊመሩ ይችላሉ፡፡
ስለ Microsoft ምዝግብ በተመለከተ የበለጠ መረጃ በ Microsoft ምዝግ ድር ጣቢያ ላ ይገኛል፡፡.
ስለሚከተለው ተጨማሪ ይወቁ
ጠቃሚ ሆነው ሊያገኟቸው (ወይም ላያገኟቸው) የሚችሉ የግላዊነት መረጃዎችን ከዚህ በታች ያገኛሉ። ከዚህ ውስጥ አብዛኛው እንዲያውቋቸው የምንፈልጋቸውን የተለመዱ አሰራሮችን የሚያብራሩ ሲሆን በእያንዳንዳቸው የግላዊነት መግለጫዎች ላይ ማተኮር እንዳለብዎ አያስቡ። እንዲሁም ከዚህ ውስጥ የተወሰነው አደባባይ ሚስጥር ነው (ለምሳሌ፣ ህግ ሲጠይቅ መረጃ ግልፅ እናደርጋለን)፣ ነገር ግን ጠበቆቻችን ምንም ቢሆን እንድንገልጸው ያስገድዱናል። እባክዎን ያስታውሱ ይህ መረጃ የእኛ ተግባራት ሙሉ መገለጫ አይደለም - ይህ ሌሎቹን ጨምሮ በሙሉ ነው፣ እርስዎ ለሚጠቀሙት እያንዳነዱ ምርትና አገልግሎት የግል ሁኔታ ደህንነት ውስጥ የበለጠ ዝርዝር መረጃ ተካቷል።
በዚህ ገጽ ላይ፤
የግል መረጃን ማጋራት እና ይፋ ማድረግ
ለሚጠቀሙት ምርት ወይም አገልግሎት የግላዊነት መግለጫ ላይ ከተገለፀው ማጋራት በተጨማሪ፣ Microsoft የግል መረጃዎችን ሊያጋራ ወይም ይፋ ሊያደርግ ይችላል፦
የግንኙነትዎን ይዘት ጨምሮ ሌሎች የግል መረጃዎችንም ልናጋራና ይፋ ልናደርግ እንችላለን፤
እባክዎ ጣቢያዎቻችን የግላዊነት ልምዳቸው ከMicrosoft ልምድ የተለየ ሊሆን የሚችል ሶስተኛ ወገን ጣቢያዎች የሚመራ አገናኝ ሊያካትቱ ይችላሉ። የግል መረጃ ከነዚህ ጣቢያዎች ውስጥ ለአንዳቸው ከሰጡ መረጃዎ ተገዢ የሚሆነው ለራሳቸው የግላዊነት መመሪያ ነው። የሚጎበኙትን የማንኛውም ጣቢያ የግላዊነት መመሪያ እንዲገመግሙ እናበረታታዎታለን።
የግል መረጃዎችን ደህንነት መጠበቅ
Microsoft የግል መረጃዎን ደህንነት ለመጠበቅ ቁርጠኛ ነው የግል መረጃዎን ፈቃድ የሌለው ሰው እንዳያገኘው፣ እንዳይጠቀመው እና ይፋ እንዳያደርገው ለመከላከል የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እና አሰራሮችን እንከተላለን። ለምሳሌ፣ የሚሰጡትን የግል መረጃዎች የተገደበ መዳረሻ ባላቸውና በቁጥጥር ስር ባሉ ቦታዎች ውስጥ ያሉ የኮምፒዩተር ስርዓቶች ላይ እናስቀምጣለን። በጣም ሚስጥራዊ የሆነ መረጃዎችን (እንደ የክሬዲት ካርድ ቁጥር ወይም የይለፍ ቃል የመሳሰሉ) በበይነ መረብ ላይ ስናስተላልፍ እንደ ደህንነቱ የተጠበቀ የሶኬት ሽፋን (SSL) ፕሮቶኮል ምስጠራን በመጠቀም እንጠብቀዋለን።
መለያዎችዎን እና የግል መረጃዎችዎን ለመጠበቅ የይለፍ ቃል ጥቅም ላይ ውሎ ከሆነ፣ የይለፍ ቃልዎን ሚስጥራዊ አድርጎ ማቆየት የእስዎ ሃላፊነት ነው። አያጋሩት። ኮምፒዩተር በጋራ የሚጠቀሙ እንደሆነ፣ መረጃዎን በቀጣይ ከሚጠቀመው ሰው ለመጠበቅ ምንጊዜም ጣቢያውን ወይም አገልግሎቱን ከመልቀቅዎ በፊት በመለያ መውጣት አለብዎ።
መረጃ የት እንደሚከማች እና እንደሚካሄድ
በMicrosoft ጣቢያዎች እና አገልግሎቶች የሚሰበሰብ የግል መረጃ በዩናይትድ ስቴትስ ወይም Microsoft ወይም አጋሮቹ፣ ተቀጣሪዎቹ ወይም አገልግሎት ሰጪዎቹ መስሪያ ቤት ባላቸው በሌሎች አገሮች ውስጥ ሊከማቹ እና ሊካሄዱ ይችላሉ። Microsoft በዩናትይድ ስቴትስ የንግድ ሚኒስቴር ከአውሮፓ ኢኮኖሚ ሕብረት አካባቢዎች፣ እና ስዊዘርላንድ ስለሚደረግ የውሂብ መሰብሰብ፣ መጠቀም እና ማስቀመጥ የተቀመጡትን የ U.S.-EU Safe Harbor Framework እና በ U.S.-Swiss Safe Harbor Framework ሕጎች አክብሮይገዛል። ስለSafe Harbor ፕሮግራምየበለጠለማወቅ፣ እናየእኛንምስክርወረቀትለማየት፣ እባክዎየሚከተለውንይጎብኙ http://www.export.gov/safeharbor/።
እንደ የ Microsoft Safe Harbor ፕሮግራም ተሳታፊነታችን፣ ከእኛ ፖሊሲዎች እና አስራሮች ጋር ሊያጋጥምዎ ለሚችል አለመግባባት መፍትሄ ለማግኘት፣ TRUSTe የተባለውን ገለልተኛ ሶስተኛ ወገን እንጠቀማለን። TRUSTe ን ማነጋገር ከፈለጉ፣ እባክዎ የሚከተለውን አድራሻ ይጎብኙ https://feedback-form.truste.com/watchdog/request።
Microsoft የግል መረጃዎን የህግ ግዴታውን ለማክበር፣ ስምምነታችንን ለማስፈጸም እና አገልግሎት ለመስጠት አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ እንዲሁም በሌሎች በርካታ ምክንያቶች የግል መረጃዎን ይይዛል። የግል መረጃዎን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ለማወቅ፣ መረጃዎን መረጃዎን በመዳረስ ላይ።
የግላዊነት መግለጫችን ላይ የተደረጉ ለውጦች
የደንበኞችን አስተያየት እና አገልግሎት ላይ የተደረጉ ለውጦችን ለማካተት በየጊዜው ግላዊነት መመሪያችንን እናዘምናለን። አንድ መግለጫ ላይ ለውጥ ስናደርግ፣ ከመግለጫው አናት ላይ ያለውን "ለመጨረሻ ጊዜ የዘመነው" የሚለውን ቀን እንከልሰዋለን። መመሪያው ላይ አንኳር ላውጦች ከተደረጉ ወይም Microsoft የግል መረጃዎን የሚጠቀምበትን መንገድ በተደረገ ለውጦች ከተደረጉ፣ እንዲህ አይነቶቹ ለውጦች ተፈጻማ ከመሆናቸው በፊት በተደጋጋሚ ማስታወቂያዎችን በመለጠፍ ወይም በቀጥታ ማሳወቂያ ለእርስዎ በመላክ እናሳውቆታለን። Microsoft እንዴት መረጃዎን እንደሚጠብቅ ለማወቅ ለሚጠቀሟቸው አገልግሎቶች እና ምርቶች በየጊዜው የግላዊነት መግለጫቸውን እንዲያዩ እናበረታታዎታለን።
እኛን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ
Microsoft Privacy, Microsoft Corporation, One Microsoft Way, Redmond, Washington 98052 USA
በክልልዎ ወይም በአገርዎ የMicrosoft አገልግሎት ሰጪን ለማግኘት፣ http://www.microsoft.com/worldwide/።
FTC ጉዳይ መነሳሳት
የቤት ደህንነት
Trustworthy Computing